Fana: At a Speed of Life!

በሴቶች 800 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉበት የሴቶች 800 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ሌሊት 10 ሰዓት ከ35 ላይ ይካሄዳል፡፡
በውድድሩ አትሌት ደርቤ ወልተጂ፣ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ እና አትሌት ሀብታም አለሙ ይሳተፋሉ፡፡
ትናንት በተካሄደው የሩብ ፍጻሜ ውድድር÷ ከምድብ አንድ አትሌት ደርቤ ወልተጂ አንደኛ፣ ከምድብ አራት አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ሁለተኛ እንዲሁም ከምድብ አምስት ደግሞ አትሌት ሀብታም ዓለሙ ሁለተኛ በመሆን ለግማሽ ፍጻሜ መድረሳቸው ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.