Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የህዝቦችን ደህንነት በማረጋገጥ ልማትን ማስቀጠል እንዲቻል በተደራጀ ዕቅድ መመራት አለብን – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና የፓርቲውን የ2014 የአፈፃፀም ግምገማ እና የ2015 እቅድ ፎረም በአዳማ እየተካሄደ ነው።

በግምገማ መድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ባደረጉት ንግግር ፥ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ፣ የህዝቦችን ደህንነት በማረጋገጥ ልማትና ዕድገትን ለማስቀጠል ወጥነት ባለው አሰራርና በተናበበ ዕቅድ መመራት አለብን ብለዋል።

አቶ ሽመልስ በክልሉ የሚስተዋሉትን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር እጦት አንስተዋል።

የ2015በጀት ዓመት የክልሉ የልማት ዕቅድ፣ የኑሮ ውድነት፣ የወጣቶች የስራ አጥነት ችግሮች እንዲሁ በመድረኩ ትኩረት የሚደረግባቸውና ቀጣይ በአፈፃፀም ተለይተው አቅጣጫ እንደሚሰጥባቸው ገልጸዋል።

ባለፉት ሦስት ወራት የአፈፃፀም ክንውኑ በተቀመጠው እቅድ ልክ ስለመሆኑ፣ አቅጣጫና አሰራሩ ተጠብቆ ስለመካሄዱ፣ በአፈጻጸም ሂደቱ የነበረው ቁርጠኝነት፣ የታዩ ክፍተቶችና ችግሮችን ለመፍታት በተለይም ህዝቡን ከማሳተፍና የሃብት ብክነትን ከመቀነስ አንጻር ያለው ሁኔታ በመድረኩ እንደሚገመገም አስታውቀዋል።

ሌብነትን ከመከላከልና በህዝባዊ መድረኮች የተነሱ ጉዳዮችን በባለቤትነት ከመፈፀምና ከማስፈፀም አንፃር በትክክል በመፈተሽ ቀጣይ አቅጣጫ እናስቀምጣለን ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.