በአማራ ክልል በኢንቨስትመንት ላይ ያሉ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችል ምክክር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በኢንቨስትመንት ላይ ያሉ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችል ምክክር ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በተገኙበት ተካሂዷል ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ከደሴ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ ከደቡብ እና ሰሜን ወሎ ዞን የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ከኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ባለሃብቶች ጋር ነው በኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ ያተኮረ ውይይት በደሴ ከተማ ያካሄዱት።
በኢንቨስትመንት፣ በመሠረተ ልማትና የክልሉን ሰላም በዘላቂነት ማረጋገጠጥን አስመልክቶ ለተነሱ ጥያቄዎች ዶክተር ይልቃል ከፋለ ምላሽ ሰጥተዋል።
ውይይቱ በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
በአንድነት ናሁሰናይ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!