Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያው ተጫዋች አሌክስ ተሰማ ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የመከላከያ ስፖርት ክለብ ተጫዋቹ አሌክስ ተሰማ ለአንድ አመት በማንኛውም ውድድር እንይዳሳተፍ መወሰኑን  አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን  በኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ውድድር ላይ ባደረገው ምርመራ አትሌት አሌክስ ተሰማ የተከለከለ አበረታች ቅመም መጠቀሙን የሚያመላክት ውጤት ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ በተጫዋቹ ጊዜያዊ እገዳ በመጣል  በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ምርመራ ሲያካሂድ የቆየ ሲሆን ተጫዋቹ ካቲኖን የተባለውን የተከለከለ አበረታች ቅመም የተጠቀመ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

በዚህም መሰረት የይግባኝ ሰሚው አካል ጉዳዩን ሲመረምር እና ሲያከራክር ቆይቶ ተጫዋቹ ጥፋተኛ በመሆኑ ለአንድ ዓመት በማንኛውም ውድድር እንደይሳተፍ ውሳኔ ማሳለፉን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

የወልቂጤ ከተማ ክለብ ተጫዋቹ ሲልባቫይን ግቦሆ የተከለከለ አበረታች ቅመም ተጠቅሞ በመገኘቱ ቀደም ሲል በፊፋ ቅጣት ተላልፎበት እንደነበር ከኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.