Fana: At a Speed of Life!

ቤተክርስቲያኗ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ20 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ወገኖች የ20 ሚሊየን 863 ሺህ ብር ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ አደረገች፡፡

ቤተክርስቲያኗ ከኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ነው ድጋፉን ያደረገችው ።

የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እርዳታና ልማት ማህበር ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ ፥ የልማት ድርጅቶቹ ከአሁን ቀደምም በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ድጋፉም ጤፍ፣ ባቄላ እና አልሚ ምግቦችን ያካተተ ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

በድጋፉ 20 ሺህ 842 የተፈናቀሉ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውንና መሰል ድጋፎችን በቀጣይ እንደሚያደርጉም ከከተማው ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.