የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ከኦሮሚያ ክልል ከተውጣጡ አባ ገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

October 29, 2019

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከአባ ገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያዩ።

በሀገሪቱ እንዲሁም በኦሮሚያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት ትናንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በስብሰባው ላይም ከሁሉም የኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ አባ ገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሴቶች እና ወጣቶች ተወካዮች ጋር ተሳትፈዋል።