ወደ አዳማ ከተማ በመግባት ላይ የነበረ 4ሺህ 603 ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መነሻውን መተሐራ አድርጎ ወደ አዳማ ከተማ በመግባት ላይ የነበረ 4ሺህ 603 ጥይት በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
1 ሺህ 828 የክላሽ እና 2 ሺህ 775 የብሬን ጥይቶች በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞችና በፌዴራል ፖሊስ አባላት ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
ጥይቶችን የያዘው ተሽከርካሪ ለድንገተኛ ፍተሻ እንዲቆም ቢጠየቅም ፈቃደኛ ባለመሆኑ የፌዴራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ አሽከርካሪውና ግብረ አበሮቹ መኪናውን አቁመው መሰወሩም ነው የተገለጸው።
ወንጀለኞቹ ለጊዜው ቢሰወሩም የፌዴራል ፖሊስና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመሆን ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ለመዋል ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!