Fana: At a Speed of Life!

በአዳማ 19 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች እና 3 ነጥብ 4 ኪሎ ግራም ወርቅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 19 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚገመት የተለያዩ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች እና 3 ነጥብ 4 ኪሎ ግራም ወርቅ ተያዘ፡፡

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ መኩሪያ ዲንቁ እንደገለጹት÷ህገ ወጥ ገንዘቡ ከአዲስ አበባ ወደ ሐረር ለማስገባት ታስቦ በመኪና ሲጓጓዝ ነው አዳማ ላይ የተያዘው፡፡

ከተያዙት ህገ ወጥ ገንዘቦች ውስጥም 328 ሺህ 181 የአሜሪካ ዶላር ፣ 46 ሺህ 815 ዩሮ እና 5 ሺህ 465 ፓውንድ እንደሚገኝበት ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 3 ነጥብ 4 ኪሎ ግራም ወርቅ ከእነ ተጠርጣሪዎቹ እንደተያዘ ሃላፊው መግለጻቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.