ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለስራ ጉብኝት ናይሮቢ ገብተዋል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ጠዋት ኬንያ ናይሮቢ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኬንያ ውጭ ጉዳይ የስራ ኃላፊዎችና በኬንያ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision