የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በአፋር ክልል በጦርነት ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልገሎት፣ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በአፋር ክልል አሸባሪው የህወሓት ቡድን ባደረሰው ጉዳት ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች አምስት ሚሊየን ብር ግምት ያለው የተለያየ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉ ለ300 የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች ለአንድ ዓመት የሚውል የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል የዕለት ደራሽ ምግብ ነክ ቁሳቁስን ያካተተ ነው፡፡
በካሳጊታ ከተማ በጦርነት የወደሙ 10 ቤቶችን መልሶ የመገንባት ስራ መጀመሩንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋን ጨምሮ የሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች በአፋር ክልል ኢሊ ውሃ ከተማ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አስቀምጠዋል።
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!