Fana: At a Speed of Life!

አመራሩ ከባለፋት ተሞክሮዎች በመማር ለቀጣዩ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ስኬታማነት መዘጋጀት አለበት -አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አመራሩ ከባለፋት ስኬቶች ተሞክሮ በመውሰድ እና ድክመቶችን በማረም ለቀጣይ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ስኬታማነት መዘጋጀት አለበት ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን አሳሰቡ፡፡
 
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በ2014 በጀት ዓመት የመንግስት እቅድ አፈጻጸም እና በ2015 በጀት ዓመት እቅድ ላይ እየመከሩ ነው፡፡
 
አቶ አሻድሊ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ያለፈውን እቅድ አፈጻጸም ገምግሞ ለቀጣይ እቅድ የማዘጋጀት ምዕራፍ ትግበራ ማከናወን የእቅዱ 50 በመቶ እደተጠናቀቀ ተርጎ ይቆጠራል።
 
የግምገማ ሂደቱ ከክልል ከፍተኛ አመራር ጀምሮ እስከ ቀበሌና ህዝብ የሚወርድ መሆኑን ጠቁመው÷ ሁሉም አመራር በሂደቱ ማለፍ እንደሚጠበቅበትም አሳስበዋል።
 
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የባለፋትን ስኬቶች እንደተሞክሮ በመውሰድ ድክመቶችን በማረም ለቀጣይ 2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ስኬታማነት መዘጋጀት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡
 
በግምገማ መድረኩ የተለዩ ጥንካሬዎች ይበልጥ የሚጠናከሩበት እና ድክመቶች የሚታረሙበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ከሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.