Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ አስታወቁ፡፡

ርዕስ መስተዳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት ÷ ምክር ቤቱ የጀጎል ቅርስን ከመጠበቅ እና ለቀጣይ ትውልድ ከማስተላለፍ አንጻር ከሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ከዚህ ባለፈም  የጀጎል ግንብ  የራሱ የሆነ አደረጃጀትና የሰው ሃይል ኖሮት በእቅድ እንዲመራ አቅጣጫ መቀመጡን ነው የገለጹት፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ  የሀረር ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለክልሉ ምክር ቤት መምራቱን  ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.