Fana: At a Speed of Life!

በ 5 የአፍሪካ ሀገራት የሚተገበረው የጋራ የሰራተኞች ፍልሰት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ 5 የአፍሪካ ሀገራት የሚተገበረው የጋራ የሰራተኞች ፍልሰት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት÷ የዜጎች መብትና ጥቅምን በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ ማስጠበቅ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ  መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በዓለም ስደተኞችን በከፍተኛ ቁጥር ከሚያስተናግዱ ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን የገለፁት ሚኒስትሯ፥ ስደተኞችን በተመለከተ በአህጉር እና በቀጠናው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትብብር ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ይህን ከግምት በማስገባት የአፍሪካ ህብረት የሠራተኞች ፍልሰት አስተዳደርን ለማሻሻል ያለመ በአምስት የአፍሪካ ሀገራት በሙከራ ደረጃ የሚተገበር የጋራ የሰራተኛ ፍልሰት መርሐ ግብር መዘጋጀቱንም ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ፣ ካሜሮን፣ ሞሮኮ፣ ኮትዲቯር እና ማላዊ ማላዊ የሚተገበረው የጋራ የሠራተኞች ፍልሰት መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩንም አስታውቀዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን፣ የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት፣ የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና ሌሎች አጋር አካላት መርሐ ግብሩ እውን እንዲሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሚኒስትሯ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.