Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በፈተናዎች ውስጥ ሆና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት አበረታች ነው- ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ሆና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የዘርፉ ምሁራን ገለጹ፡፡

የግብርና ምጣኔ ሃብት ተመራማሪዎች ዶክተር ከተማ በቀለ እና ዶክተር ስሜነህ ቢሴ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ኮቪድ-19 ፥ የውስጥ አለመረጋጋት እና የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ተፅዕኖዎች የምግብ ዋስትና ላይ አደጋ መደቀናቸውን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ መሰል ተፅዕኖዎችን ተቋቁማ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያደረገች ያለው ጥረት ዕውቅና ሊሰጠው የሚገባ ተግባር  ነው ብለዋል ምሁራኑ።

የግብርናውን ዘርፍ  ይበልጥ ለማዘመንም በቀጣይ ተጨማሪ ስራዎች እንደሚያስፈልጉ ነው ተመራማሪዎቹ የጠቆሙት።

የአግሮ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎቹ ግብርና በስፋት ባልተሰራባቸው አካባቢዎች ያሉ ዕድሎችን መጠቀም እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተገቢው ሁኔታ ለመቅረፍ ዘርፉ በሙያተኞች እንዲመራ እና እንዲደገፍ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግም አስረድተዋል፡፡

በአወል አበራ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.