Fana: At a Speed of Life!

ለዓለም አቀፉና ለብሔራዊ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔዎች ስኬት እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶች አበረታች ናቸው – የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዓለም አቀፉና ለብሔራዊ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔዎች ስኬት እስካሁን እየተደረጉያሉ ዝግጅቶች አበረታች መሆናቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ÷ ኢትዮጵያ ከህዳር 19 ቀን 2015 እስከ ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ለምታካሂደው የዓለም አቀፉ የበይነ መረብ ጉባዔ ቅድመ ዝግጅት እና ሐምሌ 28 ቀን 2014 ለሚካሄደው የብሔራዊ ኢንተርኔት አስተዳደር ጉባዔ አስመልክቶ ከአዘጋጅ ኮሚቴዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
የዓለም አቀፉ ኢንተርኔት አስተዳደር ጉባዔ እንዲሁም ብሔራዊ የኢንተርኔት አስተዳደር ዝግጅት የተከናወኑ ተግባራት እና ቀሪ ተግባራትን እንዲሁም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ የዝግጅት ኮሚቴ አባላት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት መደረጉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ዶክተር በለጠ ሞላ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ በመስሪያ ቤቱ በኩል እስካሁን እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶች አበረታች ናቸው።
በቀጣይ የተቋሙ የበላይ አመራር ትኩረት የሚሰጣቸውን በመለየት ቅድመ ዝግጅቱን ለመደገፍ በትኩረት ይሠራል ብለዋል፡፡
ሐምሌ 28 ቀን 2014 ለሚካሄደው የመጀመሪያው የብሔራዊ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ÷ ዜጎች በበይነ መረብ አስተዳደር ላይ ግንዛቤ የሚጨብጡበት መሆኑም ተገልጿል፡፡
ብሔራዊ ጉባዔው ለቀጣዩ ዓለም አቀፍ የበይነመረብ አስተዳደር ጉባዔ መንደርደሪያ እንዲሆን ትኩረት እንደሚሰጠውና በሙሉ አቅም እንደሚደገፍ አስታውቀዋል፡፡
የሚመለከታቸው የተቋሙ ኃላፊዎች፣ አጋርና ባለ ድርሻ አካላትም የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ መመሪያ ሰጥተዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.