Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሰርጌይ ላቭሮቭ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሚኖራቸው ቆይታ በሩሲያ እና ኢትዮጵያ መካከል ስላለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ላቭሮቭ ከአፍሪካ ሀገራት ዲፕሎማቶች ጋር በሚያደርጉት ውይይት በሩሲያ እና በአፍሪካ ሀገራት መካካል ያለውን ግንኙነት እና ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ እንደሚመክሩም ታውቋል፡፡

#Ethiopia #Russia #FanaUpdates

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.