Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ በታዳሽ የኃይል አማራጮች ላይ ይበልጥ እንድትሠራ የናሚቢያው ፕሬዚዳንት አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ አፍሪካን ከታዳሽ ኃይል አረንጓዴ የኃይል አማራጮችን የመጠቀም ጉዳይ ሊያሳስባት እንደሚገባ የናሚቢያው ፕሬዚዳንት ሃጌ ጂንጎብ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ጂንጎብ ይህን ያሉት 2ኛው የአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ኢኒሼቲቭ በጉዳዩ ላይ ለመምከር በጠራው ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ፕሬዚዳንቱ ÷ የሃይድሮጂን ፣ የንፋስ ፣ የፀሐይ እና ሌሎች የታዳሽ ኃይል ምንጮችን ለመጠቀም የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ዕውን ለማድረግ በአፍሪካ የኃይል አስተዳደር ፖሊሲ እና የቁጥጥር ማሻሻያዎችን መተግበር ወሳኝ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የአፍሪካ ሀገራት ለታዳሽ የኃይል አማራጭ ጥያቄ በህብረት እንዲቆሙና ለችግሮቻቸውም አፍሪካዊ መፍትሔ እንዲፈልጉም ጠይቀዋል።

ናሚቢያም በዝቅተኛ ወጪ የታዳሽ ኃይል ልማትን ለማሳካት በትኩረት እየሰራች መሆኗን ፕሬዚዳንቱ የጠቆሙ ሲሆን፥ የሃይድሮጂን ማምረቻ ማዕከል በማቋቋምም በአፍሪካ በዘርፉ ቀዳሚ ለመሆን ማቀዷን ነው የጠቆሙት።

አፍሪካ ከተባበረች በዓለም አቀፉ የኃይል አቅርቦት ገበያ ላይ ቀዳሚ የመሆን ዕድል እንዳላትም ማስገንዘባቸውን የሲጂቲ ኤን ዘገባ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.