Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የጋዝ ፍጆታቸውን ለመቀነስ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የኢነርጂ ሚኒስትሮች ትናንት በብራሰልስ ባካሄዱት ስብሰባ የጋዝ ፍጆታቸውን በ15 በመቶ ለመቀነስ ተስማምተዋል።
ስምምነቱ የጋዝ ፍጆታ ቅነሳውን የግድ የሚያደርጉ ልዩ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
የቅነሳ ድንጋጌው ሊነሳ የሚችለው የህብረቱን አባል ሀገራት መሪዎች ባሳተፈው ምክር ቤት ከፀደቀ በኋላ ብቻ መሆኑም ነው የተጠቆመው፡፡
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ የጋዝ ፍላጎትን ለመቀነስ ሁሉንም አግባብነት ያላቸው አገራዊ ጉደዮችን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
የህብረቱ ሚኒስትሮች እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት የሩሲያው ጋዝ አቅራቢ ድርጅት ጋዝፕሮም በወሳኙ የኖርድ ስትሪም አንድ የጋዝ መስመር ላይ ያለውን የጋዝ አቅርቦት ወደ 20 በመቶ እንደሚቀንስ መግለጹን ተከትሎ ነው።
ከዚህ በተጨማሪም ጋዝፕሮም የሁለተኛውን የሲመንስ የጋዝ መስመር ሥራ እንደሚያቆምም ሰሞኑን አስታውቋል።
የአቅርቦት ቅነሳው አገራዊ ደህንነትን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የተወሰደ እርምጃ እንደሆነና ጥገና ለማድረግ በሚል ምክንያት የጋዝፕሮም የጋዝ መስመር መቋረጡም በህብረቱ አባል ሀገራት ዘንድ ሌላ ትርምስ አስከትሏል፡፡
ሩሲያ በግልፅ መተማመን እንዲጓደል፣ ዋጋ እንዲጨምር እና የአውሮፓ ህብረት አንድነትን ለማዳከም እየሰራች መሆኗን አንስተዋል።
የአውሮፓ የኃይል ኮሚሽነር ካድሪ ሲምሰን፥ ይህ የሩሲያ አሰራር ሊለወጥ እንደማይችል ገልጸው፦ የጋዝ አቅርቦቱ በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ እንደሚችል እናውቃለን ሲሉም መናገራቸውን የአርቲ እና ሲጂቲኤን ዘገባ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.