የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ለአትሌቲክስ ቡድናችን አቀባበል ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ለአትሌቲክስ ቡድናችን አቀባበል ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ደማቅ ውጤት ላስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የልዑካን ቡድን አባላት አቀባበል ሲባል ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ይፋ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ የሚገባ ሲሆን÷ ለቡድኑ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡
በአቀባበሉ ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚደረጉ ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ግብረ ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ለአትሌቲክስ ቡድኑ አባላት ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ደማቅ አቀባበል የሚደረግ ሲሆን÷ የአትሌቲክስ ቡድኑ ካረፈበት ስካይላይት ሆቴል ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ በአጀብ በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ስለሚጓዝ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ግብረ ኃይሉ ማስታወቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!