የሀገር ውስጥ ዜና

የመዲናዋ ካቢኔ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶችና ለልዑካን ቡድኑ የተለያዩ ሽልማቶች እንዲሰጥ ወሰነ

By Feven Bishaw

July 27, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደ 18ኛው ዓለም ዐቀፍ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶችና ልዑካን ቡድኑን ለማመስገን የተለያዩ ሽልማቶችን እንዲሰጥ ውሳኔ አስተላልፏል ።

አስተዳደሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ላሳዩት ኢትዮጵያዊ ጀግንነት እና ላስገኙት ውጤት የምስጋና መርሃ ግብር ነገ እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡