Fana: At a Speed of Life!

የበጋ ስንዴ ልማት ኢትዮጵያን ከውስብስብ ችግር የሚያወጣና የሚታደግ የልማት ስራ ነው- ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የበጋ ስንዴ ልማት ኢትዮጵያን ከውስብስብ ችግር የሚያወጣና የሚታደግ የልማት ስራ መሆኑን የዘርፉ ምሁራን ገለጹ።

የግብርና ምርምር ባለሙያ ዶክተር ኤርሚያ አባተ ÷ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ኢትዮጵያ በፈተናዎች ውስጥ አሸናፊ እንድትሆን አስችሏታል ብለዋል።

የስንዴ ልማቱ በምግብ እራስን ከመቻል በተጨማሪ ለፖለቲካ ማስፈፀሚያ የሚውለውን የእርዳታ ምንጭንም ለመቀነስና ለማስቀረት የሚያስችል ጅምር ታይቶበታል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ተመራማሪው ዶክተር ዳንኤል ሙለታ በበኩላቸው÷የበጋ ስንዴ ልማት በዘላቂነት የዜጎችን ፍጆታ በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ያስችላል ብለዋል።

የስንዴ ፍላጎትን በራስ አቅም ማሟላት ለውጭ ስንዴ ይውል የነበረን ገንዘብ ለካፒታልና ኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲውል ያደርጋልም ነው ያሉት።

በቀጣይም ኢትዮጵያ በሰፊና በተደራጀ መንገድ ግብርናው ላይ በትኩረት በመስራት ሊከሰቱ የሚችሉ አለም አቀፋዊ  ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ችግሮችን ለመቋቋም ያስችላል  ብለዋል ምሁራኑ።

በሙሀመድ አሊ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.