Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ምክር ቤት የተነሱ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መብቶችና ጥቅሞችን በተመለከተ የተዘጋጀን አዋጅ አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አራተኛ ቀኑን የያዘው የአማራ ክልል ምክር ቤት በተለያዩ አዋጆች ላይ እየመከረ ነው፡፡

የክልሉ ምክር ቤቱ ከሃላፊነት የተነሱ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባላት፣ ዳኞች እና ዓቃቢያነ ህግ መብቶች እና ጥቅሞች በተመለከተ ተሻሽሎ የተዘጋጀን አዋጅ በ20 ተቃውሞ ፣ በሶስት ደምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

ምክር ቤቱ አሁን ላይ በክልሉ መንግስት ተሻሽሎ በወጣው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ እየመከረ ይገኛል፡፡

ምክርቤቱ በትናንትናው ውሎው “የተሻሻለው የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ” እና “የተሻሻለው የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ማቋቋሚያ አዋጅ”ን መርምሮ በአብላጫ ድምጽ ማፅደቁ ይታወሳል፡፡

በምንይችል አዘዘ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.