Fana: At a Speed of Life!

ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ ያደረጉት የስራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስጠብቁ ውሳኔዎች የተላለፉበት ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ ያደረጉት የስራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስጠብቁ ውሳኔዎች የተላለፉበት እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፥ የአሁኑ ጉብኝት ያስገኘው አንዱ ውጤት፥ ከሶቪየት ህብረት አስተዳደር ጀምሮ ሲንከባለል የቆየ ብድርን የሚመለከት ነው ብለዋል ።
ብድሩን ለማስተዳደር የኢትዮጵያ መንግስት በመረጣቸው ፕሮጀክቶች ላይ የሩሲያ ኩባንያዎች ተሰማርተው እንዲሰሩ ከስምምነት ተደርሷል ተብሏል።
በዚህም 162 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ያላቸው ፕሮጀክቶች በጋራ ተግባራዊ እንደሚደረጉ ገልጸዋል ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ግንኙነት ምክክር ማድረጋቸውን አስታውሰዋል።
በምክክራቸውም ሁለቱ ሀገራት በፓለቲካው መድረክ ያላቸው ጠንካራ ትስስር በኢኮኖሚ በንግድ በባህልና በኢንቨስትመንት ላይ እንዲደገም ተስማምተዋል።
በበርናባስ ተስፋዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.