በቄለም ወለጋ አሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ የሚገኘው ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል-የዞኑ ኮማንድ ፖስት
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ የሚገኘው ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ፡፡
በሀገር መከላከያ ሰራዊት የቄለም ወለጋ ዞን ኮማንድ ፖስት አዛዥ እንደገለጹት÷በአካባዊው በሚንቀሳቀሰው አሸባሪው ሸኔ ላይ በተወሰደ እርምጃ ቡድኑ ከፍተኛ ኪሳራ እደረሰበት ይገኛል፡፡
በዚህ መሰረትም ሰራዊቱ አሸባሪው ይጠቀምበት በነበረው በሰዮ ወረዳ ወርቄ ቀበሌ አካባቢ የሚገኝን የማሰልጠኛ ካምፕ በማውደም በርካታ የሽብር ቡድኑ አባላትን ሙትና ቁስለኛ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
አዛዡ የንጹሃንን ደም እያፈሰሰ ህዝቡን ስጋት ውስጥ ያስገባውን አሸባሪ ሃይል የመደምሰሱ ዘመቻው ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡