Fana: At a Speed of Life!

በዶ/ር ይልቃል ከፋለ የተመራ ልዑክ በደቡብ ጎንደር ዞን የጎርፍ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የተከናወኑ ተግባራትን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የተመራ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ ልዑክ በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራና ሊቦከምከም ወረዳዎች የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የተከናወኑ ተግባራትን ጎበኘ።

የአማራ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ በአካባቢው በክረምት ወራት በተደጋጋሚ የሚደርሰውን የጎርፍ አደጋ መከላከል የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ድጋፍ ቢሮው ካለፈው ዓመት ጀምሮ ያከናወናቸውን የጎርፍ መከላከል ሥራዎች በመመልከት የበለጠ ለማጠናከር በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራ ልዑክ በቦታው ጉብኝት አድርጓል፡፡

በነብዩ ዮሐንስ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.