የሀገር ውስጥ ዜና

ኢንተርፕራይዞች ዓለም አቀፍ ባዛር ላይ መሳተፋቸው ድንበር ተሻጋሪ ደንበኞችን ለማፍራት እንደሚያስችል ተገለጸ

By Meseret Awoke

July 29, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ውስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች ዓለም አቀፍ ባዛር ላይ መሳተፋቸው የዓለም ገበያ ውስጥ ልምድ እንዲያገኙ እና ድንበር ተሻጋሪ ደንበኞች እንዲኖራቸው ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥር ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ አምራች ኢንተርፕራይዞች ዛምቢያ ሉሳካ እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ ባዛር ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

ከሐምሌ 20 እስከ 25 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ እየተካሄደ በሚገኘው 94ኛው የአግሮ ሌዘር ኢንተርናሽናል ባዛር ላይ÷ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ በቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት እንዲሁም በግብርና ማቀነባበሪያ ዘርፎች የተሰማሩ 13 አምራች ኢንተርፕራይዞች እየተሳተፉ ነው፡፡

የሀገር ውስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች ዓለም አቀፍ ባዛር ላይ መሳተፋቸው ምርቶቻቸውን እንዲያስተዋውቁ፣ ዓለም አቀፍ ገበያው ውስጥ ልምድ እንዲያገኙና ድንበር ተሻጋሪ ደንበኞች እንዲኖራቸው ሰፊ ዕድል ይፈጥራል መባሉን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!