ጤና

አልጄሪያ የመጀመሪያዋን በኮረና ቫይረስ ሞት አስመዘገበች

By Meseret Demissu

March 12, 2020

አዲስ አበባ፣መጋቢት3፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) አልጄሪያ ከኮረና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በሀገሯ የመጀመሪያውን ሞት ማስመዝገቧን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በቫይረሱ የአንድ ሰው ሞት ከመመዝገቡም በተጨማሪ አምስት አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ገልጿል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ ፈረንሳይ ይኖሩ የነበሩ አልጄሪውያን መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

አሁን ላይ በአልጄሪያ በኮረና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 24 ደርሷል ነው የተባለው፡፡

እነዚህ ከፈረንሳይ የመጡ ዜጎች በምስራቅ አልጄሪያ በሚገኝ ሆስፒታል ገብተው ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ሚኒስቴሩ አያይዞም ሌሎች ሶስት ሰዎች ደግሞ በደቡብ ምዕራብ አልጀርስ ውስጥ በሚገኝ ብሊንዳ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ነው የተመለከተው፡፡

ከዚህ ቀደም በብሊንዳ 17 የአንድ ቤተሰብ አባላት ከፈረንሳይ በመጡ አልጄሪያውያን በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጾ ነበር፡፡

 

ምንጭ፡-ዴይሊ ኔሽን