Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ትልሞቻችንን እውን ለማድረግ እውቀት ዋና መሳሪያ ነው – ዶ/ር ዓለሙ ስሜ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ትልሞቻችን እውን ለማድረግ ትምህርትና እውቀት ዋና መሳሪያ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የሲቪክና ፖለቲካ ፓርቲዎች ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ ተናገሩ፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ድጋፍ እና ክትትል አስተባባሪዎች የ2014 በጀት ዓመት ግምገማ እና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ገለጻ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው።
ዶክተር ዓለሙ ስሜ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የብልጽግና ትልሞቻችን በሙሉ ቁመና እውን ለማድረግ ትምህርት እና እውቀት ዋና መሳሪያ መሆናቸው ጠቁመው ÷ ለዚህ ደግሞ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካባቢ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት መፈጠር አለበት ብለዋል፡፡
ሀገሪቱ የገጠማትን ፈተና ተሻግራ ወደ ብልጽግና ማማ ከፍ እንድትል እየተሠራ እንደሆነም ጠቁመዋል።
ውይይቱ ለሁለት ቀናት በሚኖረው ቆይታ÷ የሚታዩ የአፈፃፀም ክፍተቶችን በጥልቀት በመገምገም የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድን በተሳካ ሁኔታ እንዲፈፀም አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ይጠበቃል፡፡
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.