Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ አሻራ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባት ቁልፍ መሳሪያ በመሆኑ በልዩ ትኩረት ይሰራል- አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ለ4ኛው ዙር አረንጓዴ አሻራ በአንድ ጀምበር 1 ሚሊየን 700 ሺህ ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በተገኙበት ተጀምሯል፡፡

̎ አሻራችን ለትውልዳችን  በሚል መሪ ሃሳብ በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የተለያዩ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኡሞድ ÷ የአረንጓዴ አሻራ ስትራቴጂ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከልና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባት ቁልፍ መሳሪያ በመሆኑ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ የታየውን ተሳትፎ በማጠናከር በቀጣይ በክልሉ የተያዘውን ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ችግኝ የመትከል እቅድ ለማሳካት ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ በበኩላቸው÷ የምክር ቤት አባላትም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የተጀመረው የችግኝ ተከላው መርሐ ግብር በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች ተለይቶ በተዘጋጀ የተከላ ቦታ እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ አጃክ ኡቻላ ናቸው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.