ስፓርት

የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚደረግባቸው ቀናት ተራዘሙ

By Meseret Awoke

July 31, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚደረግባቸው ቀናት መራዘማቸውን ካፍ አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት በመስከረም ወር ሊደረጉ ቀጠሮ የተያዘላቸው የዋሊያዎቹ 3ኛ እና 4ኛ የምድብ ጨዋታዎች ከመጋቢት 11 እስከ 19-2015 የሚደረጉ ይሆናል፡፡

በተጨማሪ የሀገራቱ የምድቡ 5ኛ ጨዋታ ከሰኔ 5 እስከ 13 -2015 ባሉት ቀናት የሚከናወን ሲሆን ፥ የምድቡ 6ኛ መርሐ ግብር ከነሐሴ 29-2015 እስከ መስከረም 1-2016 ባሉት ቀናት እንደሚካሄድ ካፍ አሳውቋል ።

ካፍ አስቀድሞ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር አይቮሪኮስት የሚካሄደውን የ2023 አፍሪካ ዋንጫ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከሰኔ 2015 ወደ ጥር 2016 ማዛወሩ የሚታወስ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!