ስፓርት

የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ እጩዎች ዝርዝር ይፋ ሆነ

By Meseret Awoke

August 02, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ እጩዎች ዝርዝር ይፋ ሆኗል፡፡

ይፋ ከሆኑት ዕጩዎች ዝርዝርም ሦስት ፕሬዚዳንትና 26 የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ተወዳዳሪዎች እንደሚገኙበት ፌዴሬሽኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

አቶ መላኩ ፈንታ ፣ አቶ ኢሳያስ ጅራ ቦሾ እና አቶ ቶኮቻ ዓለማየሁ ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት ታጭተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!