Fana: At a Speed of Life!

ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የተሸረሸረውን የአብሮነት እሴት መልሶ ለመገንባት ትልቅ ፋይዳ አለው አሉ ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለዓመታት በልዩነት ላይ በመሰራቱ የተሸረሸረውን የአብሮነት እሴት መልሶ ለመገንባት ትልቅ ፋይዳ አለው ሲሉ የማህበራዊ ሳይንስ ምሁራን ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያውያንን አንድ ከሚያደርጉ ጉዳዮች ይልቅ በልዩነታቸው ላይ እንዲያተኩሩ በመሰራቱ ሕዝቡ በየአካባቢው እንዲታጠርተደርጎ ቆይተዋል ሲሉ ያነሱት የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሳይንስ ምሁራን፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትኩረት የተሰጠው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የላላውን አብሮነትና ማህበራዊ ትስስር ለማጠናከር የሚኖረው ዋጋ ከፍ ያለ ነው ብለዋል፡፡

ከ20 ዓመታት በላይ ከጋራ ጉዳይ ይልቅ ልዩነትን የሚያሰፋ ስራ በትምህርት ስርዓት ሳይቀር ተደግፎ በመሰራቱ አብሮነት ተሸርሽሯል ያሉት ምሁራኑ ፥ በአንድ ሀገር የሚኖሩ ግን የማይተዋወቁ ሆነው የቆዩ ህዝቦችን ለማቀራረብ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሳይንስ መምህር የሆኑት ተሾመ ደስታ እንዳሉት፥ የተጀመረው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከግለሰብ እስከ ሀገር የሚሻገር ከፍ ያለ ፋይዳ አለው፡፡

በተለይ ልዩነት ብቻ ጎልቶ ሲሰበክ በመቆየቱ የተፈጠረውን ክፍተት ለማስተካከልና ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ትልቅ ዋጋ እንዳለው አንስተዋል፡፡

የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ያለውን ዋጋ ግምት ውስጥ በማስገባት አገልግሎቱን ተቋማዊ አድርጎ ማዝለቅ ይገባል ሲሉም ምሁራኑ አስገንዝበዋል፡፡

በተስፋዬ ምሬሳ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.