ስፓርት

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የቡድኑን ዋና እና ረዳት አሰልጣኞቹን አገደ

By Tibebu Kebede

March 13, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሥራ አመራር ቦርድ በዋና አሰልጣኝ፣ ረዳት አሰልጣኞች እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ላይ ጊዜያዊ እገዳ መጣሉን አስታወቀ።

የስፖርት ማህበሩ ሥራ አመራር ቦርድ ባደረገው ስብሰባ የዋናውን እግር ኳስ ቡድን ወቅታዊ አቋም በሰፊው ከገመገመ በኋላ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል።