Fana: At a Speed of Life!

“ሐላል የምግብና ቱሪዝም ኤክስፖ” የፊታችን ሰኞ እንደሚጀምር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ”ሐላል” የምግብና ቱሪዝም ኤክስፖ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

ኤክስፖው ‘’ከኢድ እስከ ኢድ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት’’ የሚለው መርሐ -ግብር አካል መሆኑም ነው የተመለከተው፡፡

ኤክስፖውን በርካታ ቀጥር ያላቸው የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር ታዳሚዎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በኤክስፖው የምግብና መጠጥ አምራቾች፣ የግብርና ምርት አቅራቢዎች፣ ሆቴልና መስተንግዶ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች እንዲሁም የ ”ሐላል” አስጎብኚ ድርጅቶች በሥፋት ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው እንደሚቀርቡም ነው የመርሐ-ግብሩ አዘጋጅ በመረጃው ያመላከተው፡፡

የሐላል ኢንዱስትሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዕድገት እያሳየ ያለ አዲስ የንግድ አቅጣጫ ሲሆን በተለይ ከ ‘ኮቪድ 19’ ወረርሽኝ መከሰት ወዲህ በርካቶች ለ`ሐላል ምርቶች እና አገልግሎቶች`ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱ ተጠቁሟል።

በግሎባል ኢስላሚክ ኢኮኖሚ ሪፖርት መሠረት ለሐላል ምርቶችና ግልጋሎቶች ፍላጎት ያላቸው ተጠቃሚዎች መበራከታቸውን እና በአንድ ዓመት ብቻ 4 ትሪሊየን ዶላር በሚደርስ ወጪ ግዢ መፈጸማቸውን እና አገልግሎቶችን ማግኘታቸውን ከመርሐ-ግብሩ አዘጋጅ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.