ቢዝነስ

የሱዳን ባለሃብቶች የልዑካን ቡድን በትግራይ ክልል ጉብኝት እያደረገ ነው

By Tibebu Kebede

March 13, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳን ባለሃብቶች የልዑካን ቡድን በተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ጉብኝት በማድረግ ላይ ነው፡፡

ልዑኩ ለአንድ ሳምንት በሚኖረው ቆይታ በክልሉ ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች ይመለከታል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች ባለሃብቶቹ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ከክልሉ የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩም ነው የተመለከተው።

ባለሀብቶቹ በሱዳን እና በሌሎች መካከለኛው ምስራቅ ሃገራት በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ ናቸው።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision