የሀገር ውስጥ ዜና

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ለ2015 በጀት አመት ከ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ አፀደቀ

By Alemayehu Geremew

August 03, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ ዙር 1 አመት 2 መደበኛ ጉባኤ 3 ቢሊየን 405 ሚሊየን 105 ሺህ ብር ሆኖ የቀረበለትን የክልሉ መንግስት የ2015 በጀት አፅድቋል።

የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አብዱልባሲጥ አቡበከር ከተያዘው በጀት 51 በመቶ ለካፒታል በጀት እንዲሁም 49 በመቶው ደግሞ ለመደበኛ በጀት የሚውል ነው ብለዋል።

በጀቱም በዋናነት በክልሉ ከተለያዩ ገቢዎች ከሚሰበሰብ ገቢ እና ከፌዴራል መንግስት ድጎማ የሚሸፈን መሆኑን ተናግረዋል።

የፀደቀው በጀት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ14 በመቶ ብልጫ እንዳለው መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።