ስፓርት

በዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የብር ሜዳሊያ አገኘች

By Melaku Gedif

August 04, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሎምቢያ ካሊ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር የፍጻሜ ውድድር የብር ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

አትሌት ኤርሚያስ ግርማ ርቀቱን በ3 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ 24 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ሁለተኛ ደረጃን መያዝ ችሏል፡፡

በዚህም አትሌት ኤርሚያስ በሻማፒዮናው ለሀገሩ የብር ሜዳሊያ ማስገኘቱን ከአትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ ርቀት ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፈው አድሃና ካሳዬ ደግሞ 4ኛ በመውጣት ዲፕሎማ አግኝቷል፡፡