Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የስነ-ምህዳር ካርበን መቆጣጠሪያ ሳተላይት ወደ ህዋ ላከች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በሻንዚ ግዛት ከሚገኘው የሳተላይት ማምጠቂያ ማዕከል የመሬት ስነ-ምህዳር የካርቦን መቆጣጠሪያ ሳተላይት እና ሌሎች ሁለት ሳተላይቶችን በዛሬው ዕለት ወደ ህዋ ልካለች።

የካርበን መቆጣጠሪያ ሳተላይቱ የመሬት ሥነ-ምህዳርን እና የተፈጥሮ ሀብቶችን ለመከታተል፣ ሀገራዊ ዋና ዋና የስነ-ምህዳር ፕሮጀክቶችን ለመገምገም እንዲሁም ለቅየሳ እና የካርታ ስራዎች ፣ለአየር ትንበያ ፣አካባቢ ጥበቃ፣ ግብርና እና አደጋ ቅነሳ አገልግሎቶችን ይሰጣል ተብሏል።

ሳተላይቱ የእጽዋት ባዮማስን፣ የከባቢ አየር ኤሮሶልን እና ክሎሮፊል ፍሎረሰንስን በተለያዩ የርቀት ዳሰሳ ዘዴዎች መለየት እና መለካት እንደሚችል ነው የተገለፀው።

በዓለም አቀፍ  የካርበን ማስረጊያ የደን ሽፋን መረጃን ማግኘት ያስችላል የተባለለት ሳተላይቱ÷ የቻይናን የካርበን ልቀት መጠን እና ለጥረቶቿ ድጋፍ መስጠት እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

በዚህ ተልዕኮ የተወነጨፉት ሌሎች ሳተላይቶች ከዓለም አቀፍ የመርከብ ቁጥጥር እና የበረራ ሁኔታ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን የሚሰበስቡ እና ተማሪዎችም በህዋ ሳይንስ ጥናትና ምርምር እንዲሁም ምህንድስና ልምምድ ላይ እንዲሳተፉ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችሉ መጠቆሙን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.