Fana: At a Speed of Life!

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የአገራዊ ምክክሩን ሂደት የሚከታተል ቡድን አቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የአገራዊ ምክክሩን ሂደት የሚከታተል ቡድን ማቋቋሙን አስታውቋል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አገራዊ ምክክሩን አስመልክቶ ከሲቪል ማህበራት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።

ውይይቱ÷ በመጪው ህዳር ወር ሊጀመር በታሰበው አገራዊ ምክክር ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ሔኖክ መለሰ እንደገለጹት÷ የሲቪል ማህበረሰቡ አባላት ለአገራዊ ምክክሩ ስኬት ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ምክር ቤቱም ዘርፉን እንዲወክል በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የሲቪል ማህበረሰቡን በማንቀሳቀስ በምክክሩ አስተዋጽዖ እንዲያበረክት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ምክር ቤቱ ከሲቪል ማህበረሰቡ የተውጣጣና አገራዊ የምክክር ሂደቱን የሚከታተል ወይም የ’ሪፈረንስ’ ቡድን ማቋቋሙንም ገልጸዋል።

የምክር ቤቱ የፕሮግራም እና ልማት አማካሪ ዶክተር ሞገስ ደምሴ በበኩላቸው÷ ምክክሩ የአገሪቱ ዋነኛ አጀንዳ እየሆነ መምጣቱን ጠቁመው÷ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በዚህ አገራዊ ምክክር ላይ ለመሳተፍ እና የመፍትሔ አካል ለመሆን ፍላጎት ማሳየታቸውን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.