Fana: At a Speed of Life!

ነዳጅን ለታለመለት ዓላማ ለማዋል ተቋማቱ በቅንጅት ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር በመተባበር የትራፊክ አደጋ፣ የመንገድና የባቡር ትራንስፖርት ደኅንነትን ለማስጠበቅ እና በአቪዬሽን ዘርፍ በጋራ ለመሥራት እንዲሁም ነዳጅን ለታለመለት ዓላማ ለማዋል ተስማምተዋል፡፡

የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱም የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚንስትር  ዳግማዊት ሞገስ እንደገለጹት÷ ነዳጅን በትራንስፖርት ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ብቻ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ማድረግ አስቸጋሪ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖለስ ጋር የአሰራር ሥርዓት ዘርግቶ በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

መንግስት ከፍተኛ ወጪ መድቦ ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ እና ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ድጎማ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው÷ አንዳንድ ስግብግብ ግለሰቦች በወጣው የድጎማ ዋጋ መሰረት ነዳጅ እንዳይሸጥ ችግር እየፈጠሩ በመሆኑ ይህንን ችግር በጋራ መታገል ይገባል ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ  ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው÷ ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር የአቪዬሽኑን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ለአቪዬሽን ፖሊስ አባላት ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።

ሁለቱ ተቋማት በትራንስፖርቱ ዘርፍ በቀጣይ ስለሚያከናውኗቸው ተግባራት የሚያጠና እና የሚገመግም የጋራ ኮሚቴ እንደሚቋቋም መግለጻቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.