Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ 307 ሔክታር በከተማ ግብርና እየለማ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ 307 ሔክታር መሬት በከተማ ግብርና እየለማ ነው መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር መሀመድ ልጋኒ እንደገለጹት÷ በመዲናዋ በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ አነስተኛ ቦታዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ጨምሮ 307 ሔክታር መሬት በከተማ ግብርና እየለማ ነው፡፡

አርሶ አደሮችን ጨምሮ ከ350 ሺህ በላይ ዜጎች በከተማ ግብርና ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው÷ በተያዘው የ2014/15 የመኸር እርሻ ሥራ 11 ሺህ 81 ሔክታር መሬት ለከተማ ግብርና መዘጋጀቱንና ለዚህም የሚያስፈልገው የግብርና ግብዓት እየቀረበ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በከተማ ግብርና ላይ የተሰማሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት÷ በከተማ ግብርና የምግብ ፍጆታቸውን ከመሸፈን ባለፈ ተጨማሪ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን እና ከራሳቸው አልፈው ለሌሎችም መትረፋቸውን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰኔ ወር 2013 ዓ.ም “ምግባችን ከደጃችን” በሚል መሪ ቃል የመኸር የከተማ ግብርና ሥራን ማስጀመሩ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.