Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር እና ሽጉጥ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር እና 3 ሽጉጥ እንዲሁም ጥይቶች መያዙን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የገንዘብ ዝውውር በሀገር ደኅንነትና በኢኮኖሚ ላይ የሚያመጣውን አደጋ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ለፀጥታ ኃይሎች እያደረገ ያለውን ቀና ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች እና የውጭ አገር ገንዘቡ የተያዘው በህብረተሰቡ ጥቆማና በፖሊስ ክትትል መሆኑን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.