Fana: At a Speed of Life!

ኮሮና ቫይረስ ጎረቤት ሱዳን እና ኬንያ ገባ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያ የመጀመሪያዋን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ማግኘቷን አስታወቀች።

የሃገሪቱ ጤና ሚኒስትር ሙታይ ካግዌ እንዳሉት ከሳምንት በፊት ከአሜሪካ የመጣች ሴት የቫይረሱ ተጠቂ መሆኗ ተረጋግጧል።

አሁን ላይም ግለሰቧ በጥሩ ጤንነት ላይ የምትገኝ ሲሆን በለይቶ ማቆያ ክፍል ውስጥ ክትትል እየተደረገላት ነው ብለዋል።

በተያያዘ ዜናም ጎረቤት ሱዳን እና ጊኒም የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

በሱዳን የቫይረሱ ተጠቂ የሆነው ግለሰብ የ50 አመት ጎልማሳ ሲሆን፥ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በወሩ መጀመሪያ ጉዞ ማድረጉን የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ግለሰቡ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት መዳረጉንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

ጋና እና ጋቦንም የመጀመሪያዎቹን የቫይረሱን ተጠቂዎች ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.