ፍርድ ቤቱ በእነ አቶ በረከት ስምኦን ላይ ዓቃቤ ህግ ያቀረባቸውን ክስ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ በረከት ስምኦን ላይ ዓቃቤ ህግ ያቀረባቸውን ክስ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለሚያዚያ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ቀጠረ።
ፍርድ ቤቱ በዛሬው እለት በዋለው ችሎት በዓቃቤ ህግ እና በተከሳሾቹ መካከል የነበረው ክርክር መጠናቀቁን አስረድቷል።
በመሆኑም ክሱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ያለውን የከሳሽና የተከሳሾች የቃልና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ለሚያዚያ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
በዓቃቤ ህግ የቀረበውን የቃል እና የሠነድ ማስረጃዎች እንዲሁም በተከሳሾች የቀረበው የሰነድ እና የቃል ማስረጃዎችን ለመመርመር ብዙ ጊዜ እንደሚስፈልገውም ፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
አቶ በረከት በበኩላቸው ካለባቸው የጤና ችግር አንፃር የፍርድ ውሳኔው በቀጠሮ ቀን እንዲታይላቸው ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱም ውሳኔውን ለማፋጠን ምርመራውን በተገቢው ሁኔታ እንደሚመለከተው አስረድቷል።
በናትናኤል ጥጋቡ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision