ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ኬንያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በናይሮቢ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ።
በኬንያ ናይሮቢ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ፕሬዚዳንቷ በኬንያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ አባላት ጋር በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸው በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር እየተደረገ ባለው ድርድር ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ፕሬዚዳንቷ በዚህ ወቅት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን እየተሳተፉበት ያለ የህዝብ ፕሮጀክት መሆኑን አስረድተዋል።
በውጭ የሚኖሩ ዜጎች እስካሁን ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ፕሬዚዳንቷ የበለጠ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያውያኑ በግድቡ የድርድር ሂደት ላይ መንግስት የያዘውን አቋም አድንቀው፥ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል መግባታቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ መላክታል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision