Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት የ4ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ አካል የሆነ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እንዲሁም ቱሪዝም ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አመራሮችና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ አመራሮችና ሠራተኞች በአምቦ ዩኒቨርስቲ ወሊሶ ካምፓስ የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተክለዋል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች ሁለተኛውን ዙር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በእንጦጦ ፓርክ አከናውነዋል፡፡

የተከሉትን ችግኞች በቀጣይ በትኩረት እንደሚንከባከቡ ከየተቋማቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም ቱሪዝም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመሆን እንጦጦ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቅርስ ባላደራ ማኅበር በሚያስተዳድረው ሥፍራ ችግኝ ተክለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.