የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌ ብር አዲስ የፋይናንስ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እያካሄደ ነው

By Mikias Ayele

August 05, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌ ብር አዲስ የፋይናንስ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እያካሄደ ነው።

በስካይላይት ሆቴል እየተካሄደ ያለው መርሐ ግብር “የፋይናንስ አገልግሎት ለሁሉም” በሚል ሶስት የፋይናንስ አገልግሎትን በቴሌብር የሚያካትት ነው ተብሏል።

የፋይናንስ አገልግሎቱ ቴሌብር መላ በሚል የብድር፣ ቴሌብር ሳንዱቅ የቁጠባ እና ቴሌብር እንደኪሴ በሚል ደግሞ የኦቨር ድራፍት አገልግሎት የሚሰጥበት መሆኑም ታውቋል።

በታሪኩ ለገሰ