የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ባጫ ደበሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንት ኡሁሩ አቀረቡ

By Mekoya Hailemariam

August 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ባጫ ደበሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ አቀረቡ።

አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅትም፥ ረዥም ዓመታትን ያስቆጠረውን እና ባለ ብዙ መልክ የሆነውን የኢትዮጵያና ኬንያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛነታቸውን ገልፀዋል።