Fana: At a Speed of Life!

የህጻናትን ደህንነት በዘላቂነት ለማስከበር የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል-ሚኒስትር ዴኤታ አለሚቱ ኡሞት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህጻናትን መብት እና ደህንነት በዘላቂነት ለማስከበር የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አለሚቱ ኡሞት ገለጹ፡፡

ኬር ኢትዮጵያ የህጻናትን መብት እና ደህንነት ማስጠበቅ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የምክክት መድረክ አካሂዷል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይሚኒስትር ዴኤታ አለሚቱ ኡሞት÷የህጻናትን መብት እና ደህንነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የሚኖረው የባለድርሻ አካላት ትብብርም በኢትዮጵያ ለህጻናት መብት እና ደህንነትን ተግዳሮት ለሆኑ ጉዳዮች ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የህጻናትን መብትና ደህንነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ ባለ ብዙ ድርሻ አካላት የሚሳተፉበት እና የቴክኒክ ቡድን ያለው ስርዓት ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሂዷል፡፡

የሚቋቋመው ቡድንም ለህጻናት ደህንነት የሚውል ሃብት ማሰባሰብ፣ የመፍትሄ ሃሳቦችን መጠቆም፣ የተሻሉ የፖሊስ ተሞክሮችዎን ማምጣት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የራሱን ሚና እንደሚያበረክት ተመላክቷል፡፡

በህጻናት እድገት ላይ የተናጠል ስራ አመርቂ ውጤት አያስመዘግብም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ÷ኬር ኢትየጵያ እና መሰል ድርጅቶች ከሚኒስቴሩ ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ በኢትዮጵያ የህጻናትን መብት እና ደህንነት የሚገዳደር ስር የሰደደ ችግር እንደሆነ መገለጹን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.