Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮናን 3ኛ በመሆን አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሎምቢያ ካሊ የተካሄደውን የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከዓለም ሶስተኛ በመሆን አጠናቀቀች።

በውድድሩ ኢትዮጵያ 6 የወርቅ፣ 5 የብር እና 1 ነሃስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

በሻምፒዮናው ማጠናቀቂያ እለት አራት ወርቅ እና ሁለት የብር ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

በሻምፒዮናው አሜሪካ 7 የወርቅ፣ 4 የብር እና 4 የነሐስ በአጠቃላይ 15 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አንደኛ ሆናለች።

ጃማይካ 6 ወርቅ፣ 7 የብር እና 3 የነሐስ በአጠቃላይ 16 ሜዳሊያዎች አግኝታ ሁለተኛ ሆናለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.